በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ጽ/ቤት የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
1. የደንብ ልብስ፣ 2. አላቂ የህክምና እቃ፤ 3. አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ 4. የፅዳት እቃዎች፣ 5. ሌሎች የእጅ መሳሪያዎች፣ 6. ቋሚ እቃዎች ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት፣ የቫት ከፋይ ሰርተፍኬት ያላቸው በዕቃና አገልግሎት ግዥ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ የጨረታውን 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ካደራጀው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ከላይ ለተዘረዘሩ እቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በት/ቤቱ ቢሮ ቁ. 5 በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ድምሩን ጨምረው በግልጽ በመሙላትና በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውንና ኮፒውን ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃ ሁሉ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል።
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት 10ኛ ቀን ላይ ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- በጨረታው ሂደት ቅሬታ ያለው አካል ጨረታው ከተከፈተ እስከ 3 ቀን ድረስ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
- የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈው እቃ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል ግዴታ ሲሆን አልዋዋልም ቢል ያስያዘው ሲፒኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- ተጫራቾች ባቀረቡት ናሙና መሰረት አሸናፊ ሲሆኑ ያሸነፉበት ዕቃ በናሙናው መሰረት ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች አሸናፊ ሲሆኑ ያሸነፉበትን ዕቃ የጨረታው ማስከበሪያ 10% ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 442 60 36 መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሳሪስ የገበያ ማዕከል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ሬስ ኢንጅነሪንግ ጀርባ ቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የቡልቡላ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
