በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ፤ የጽ/መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ብትን ጨርቅ፣ ጫማዎችን እና የውጭ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ቁሳቁሶች ማለትም የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ፣ የጽ/መሳሪያ፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ብትን ጨርቅ፣ ጫማዎችን እና የውጭ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ለ2018 ዓ.ም የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያለውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ አሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም የማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 400.00 /አራት መቶ ብር/ የኢትዮጵያ ብር ለሚወዳደሩበት ሰነድ በመግዛት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጠየቁትን ዕቃዎች በተጠየቀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት መሙላት ያለባቸው ሲሆን የስፖርት ትጥቆች እና ሳንፕል በቀረበባቸው ዕቃዎች መስ/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጨረታ ብር /የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ፣ የጽ/መሳሪያ 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/፣ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁስ ብር 20,000.00፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች 20,000.00 ብር፣ የጽዳት እቃዎች ብር 10,000.00 ብትን ጨርቅ 6,000.00፣ ጫማዎች 10,000.00፣ የውጭ ፈርኒቸር 10,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.አ /ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በመሙላትና በመፈረምና በታሸገ ፖስታ በማድረግ የመ/ቤቱን አድራሻ፣ የድርጅቱን አድራሻ፣ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ እለት 3፡30 ታሽጎ 4፡00 /አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻለው እስከ 15ኛው ቀን 11:30 ድረስ ብቻ ነው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ዝግ /በዓል/ የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎት የሚያወዳድር ስለሆነ በአንድ ምድብ ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ ሳይሞሉ መተው አይቻልም በሎት ያልሞላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለፀላቸው ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ቀርበው ውል መያዝ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0587760443 መደወል ይችላሉ፡፡
በምስ/ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
