Tender Detail

Tender Details


የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ከዘ/ስርጭት ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ፣ ሎት 5 የስፖርት ዕቃ፣ ሎት 6 የሙዚቃ መሣሪያ፣ ሎት 7 የመኪና እቃ እና ሎት 8 ቋሚ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ እና ለደሴ ትም/መሣ/ከዘ/ስርጭት ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ ሎት 4 የህንፃ መሣሪያ፣ ሎት 5 የስፖርት ዕቃ፣ ሎት 6 የሙዚቃ መሣሪያ፣ ሎት 7 የመኪና እቃ እና ሎት 8 ቋሚ ዕቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1- 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 007 ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደሴ መም/ትም/ኮሌጅ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 007 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ23/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 07/03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 007 07/03/2018 ዓ.ም በ8፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን በ8፡30 ጨረታው ይከፈታል ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ቀን ይተላለፋል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 007 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0333124220 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የጽህፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ የህንፃ መሣሪያ፣ የስፖርት ዕቃ፣ የሙዚቃ መሣሪያ፣ በተመለከተ ጨረታው የሚወዳደረው በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ ስለሆነ አንድም ዕቃ ቢሆን ክፍት ማድረግ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል።
  • እንዲሁም የመኪና እቃን በተመለከተ ጨረታው የሚወዳደረው በነጠላ ዋጋ ነው።
  • በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖር በጥንቃቄ ይሙሉ።
  • ጨረታውን ሲሞሉ ቫትን አካተው መሙላት አለባቸው።
  • ሳምፕል ያቀረብናቸውን ዕቃዎች ሳምፕሉን በማየት እንድትሞሉ እናሳስባለን።

 

የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ

 

Save Tender