በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ፣ ህትመትና የህትመት ውጤቶች፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጀንት፣ የመኪና ጎማ ግዥ፣ በወግዲ ከተማ የማህበረሰብ መዝናኛ ግንባታ፣ ግንባታ፣ በወግዲወረዳ ውስጥ ለሚገነባ ሸድ ግንባታ የእጅ ዋጋ ማስገንባት ማስገንባት እና የህንፃ መሳሪያ ዕቃ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን በወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የጽ/መሳሪያ፣ ህትመትና የህትመት ውጤቶች፣ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ ክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጀንት፣ የመኪና ጎማ ግዥ፣ በወግዲ ከተማ የማህበረሰብ መዝናኛ ግንባታ፣ ግንባታ፣ በወግዲወረዳ ውስጥ ለሚገነባ ሼድ ግንባታ የእጅ ዋጋ ማስገንባት ማስገንባት እና የህንፃ መሳሪያ ዕቃ በሀገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ጽ/ቤታችን ይጋብዛል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑ የታደሰና ህጋዊ ፈቃድ ያለውና የንግድ ስራ ዘርፉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ነምበር ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
- የግዥ መጠን ከ200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተወዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ ላይ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው የንግድ ስራ ፍቃድ ኮድ መሰረት ንግድ ፈቃዳቸውን ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዕቃ ግዥ እስከ 15ኛው እና ለግንባታ ደግሞ 21ኛው ቀን ድረስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመፈረምና የድርጅቱን አድራሻ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመፈረም ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለእቃ ግዥ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚያው በ16 ኛው ቀን ጨረታው 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ለግንባታ ደግሞ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ22ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥና ን/አስ/ቡድን ቢሮ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦሪጂናል ፖስታ እና ኮፒ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነት በተገለጸላቸው ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መግባት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ለጽ/መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣ ለህትመትና የህትመት ውጤቶች ብር 2,000 (ሁለት ሺህ ብር) ፣ ለሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ፣ ለኤሌክትሮኒክስ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣ ለፈርኒቸር ብር 1,200 (አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) ፣ ለክሎሪንና የውሃ መመርመሪያ ሪኤጀንት ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ፣ ለመኪና ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለመዝናኛ ግንባታውና ለሸድ ግንባታ የእጅ ዋጋ የሞሉትን 1.5 ፐርሰንት፣ እና ለህንፃ መሳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ነጠላ ዋጋም ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ማድረግ አለበት ለግንባታው ግን ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይገባዋል ካለው ደግሞ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ውድድሩ በጥቅል ድምር (ሎት) መሆኑን እንዲያውቁትና የሁሉንም እቃዎች ዋጋ መሙላት የሚጠበቅበዎት መሆኑን አይዘንጉ።
- ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ፀንቶ የመቆያ ጊዜ 30 ቀን መሆኑ ይታወቅ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደ/ወሎ ዞን የወግዲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
