በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በሰ/ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የቀወት ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት (1) ጽ/መሣሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2100፣ ሎት (2) የጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1200፣ ሎት (3) ህትመት ጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000፣ ሎት (4) ኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000፣ ሎት (5) የቤትና የቢሮ እቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ ብር 4000፣ ሎት (6) ህንጻ መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000፣ ሎት (7) የተዘጋጀ ደንብ ልብስ ጨረታ ማስከበሪያ ብር 1100፣ ሎት (8) ብትን ጨርቅ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1100
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ1-3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታው ውድድር በጥቅል መሆኑን አውቀው ጨረታውን መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ በተገለጸው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆይበት 40 ቀን በኋላ ለተጨማሪ 20 ቀን ጸንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቀው የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቹ ለእያንዳንዱ ሎት ጨረታ ሰነዱን የማይመለሰ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 11 ማግኘት ይቻላል።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው እለት 3፡30 ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 664 0059/ 0598/ ማግኘት ይችላሉ።
የቀወት ወረዳ ፍርድ ቤት
