Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Addis Ababa Revenues Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር፡- 002/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሚከተለውን አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት አንድ፡- የሰራተኛ ዩኒፎርም
  • ሎት ሁለት፡- የድንብ ልብስ/ ደረጃውን የጠበቀ ሙሉ ሱፍ፣ 70% ሱፍ 30% ፖሊስተር ከሆነ ማቴሪያል የተሰራ ጨርቅ (ኮትና ሱሪ፣ ኮትና ለጉርድ ቀሚስ ወዘተ)
  • ሎት ሶስት፡- የጽሕፈት መሣሪያዎች
  • ሎት አራት፡- የጽዳት እቃዎች
  • ሎት አምስት፡- የሕትመት ውጤቶች
  • ሎት ስድስት፡- የአይቲ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት ሰባት:- የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች
  • ሎት ስምንት፡- የተሽከርካሪ እቃዎች
  • ሎት ዘጠኝ፡- ፓርቲሽን ሥራ እና ተያያዥ አገልግሎቶች

በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል “አንድ ኦርጅናል ኮፒ” እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር “አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም፤ አድራሻ እና ማሕተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ በኤንቨሎፕ በማቅረብ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን (በሚቀጥለው የሥራ ቀን) በ4፡00 በግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 202 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን እሑድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ጠቅላላ ከሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ ለሎት አንድ 2%፣ ለሎት ሁለት 2%፣ ለሎት ሶስት 2%፣ ለሎት አራት 2%፣ ለሎት አምስት 2%፣ ለሎት ስድሰት 2%፣ ለሎት ሰባት 2%፣ ለሎት ስምንት 2% የሚወዳደሩበት ሎት በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያያዘው ማቅረብ አለባቸው። CPO መሰራት ያለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በሚል አድራሻ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ማስታውቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜ እስከ 11፡00 ሰዓት ጨምሮ በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሜክሲኮ ገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ (ቫት) ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ/ቫት/ በፊት መሆኑን መግለጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያልተገለፁ ከሆነ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀባቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀው በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ከማስገባታቸው በፊት ናሙናዎችን ለግዥ እገልግሎት ቡድን ማስገባት አለባቸው።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለተጨማሪ መረጃ፤

በስልክ ቁጥር፡- 0115 57 57 42 /0115 57 57 19 በመደወል ወይንም ሜክሲኮ ከገነት ሆቴል ገባ ብሎ አፍሪካ ኅብረት ፊት ለፊት አማጋ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 ግዥ አገልግሎት ቡድን በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ

 

Save Tender