በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ግዥዎች፤ የትራንስፖርት የአገልግሎት ግዥዎች እና የቄብ ዶሮ ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 04/2018
በቂርቆስ ክ/ከ/አስ/በዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ለዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት ለ 2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የቋሚ እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ የደንብ ልብስ ግዥዎች፤ የትራንስፖርት የአገልግሎት ግዥዎች እና የቄብ ዶሮ ግዥ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 3 የፅዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 4. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
- ሎት 5 የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 6 የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
- ሎት 7 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ
- ሎት 8. የቄብ ዶሮ ግዥ
በመሆኑም ተጫራቾች-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ የሥራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /tin no/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው።
- ተጫራቾች ከግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- ለወዳደሩባቸው የአገልግሎት አይነቶች የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ አቀራረብ 1 ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል 1 ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ሰነድ ኦሪጅናል እና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም 1 ሲፒኦ ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት።
- የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ላይ በሚገኘው የቂርቆስ ከፍለ ከተማ አስተዳደር አዲስ ህንፃ 3ኛ ፎቅ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን እንድ ቀን ብሎ በመቁጠር 11ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ እንደ ማሳሰቢያ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማሪዎት ሆቴል ፊት ለፊት የቂርቆስ ክ/ከ/አስ/ አዲሱ ህንፃ 9ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 0115548264 /0118-69-43-66
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፅ/ቤት
