Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት
  • Address ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡሩ መጨረሻ ከህብረት ባንክ ጀርባ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +25114709554
  • Website
  • Deadline04 Nov 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተገልጿል
  • opening date2025-11-04 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Textile, Garment & Leather , Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Merchandise , Sanitary Ware

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1. ሩዝ፣ 2. የምግብ ዘይት፣ 3 ፓስታ፣ 4. የልብስ ማጠቢያ ሳሙና፣ 5. ፈሳሽ የእቃ ማጠቢያ ሳሙና፣ 6. የእቃ ማጠቢያ ሳሙና (አጃክስ)፣ 7. የመፀዳጃ ቤት ወረቀት፣ 8. A4 የፕሪንተር ወረቀት፣ 9. ፈሳሽ የልብስ ማጠቢያ ሳሙና፣ 10. የገላ ሳሙና፣ 11. የልብስ የዱቄት ሳሙና፣ 12 ብርድ ልብስ፣ 13. አንሶላ፣ 14. ምስር ክክ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች: -

  1. በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችሉት አምራች ድርጅቶች ብቻ ሲሆኑ ከላይ በተራ ቁጥር 1፣2፣8 እና 14 (ሩዝ፣ የምግብ ዘይት፣ A4 የፕሪንተር ወረቀት እና ምስር ክክ) ለተጠቀሱ ምርቶች ከአምራች ድርጅቶች በተጨማሪ አስመጪ ወይም አከፋፋዮች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል፡፡
  3. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ቃሊቲ ጉምሩክ የባቡሩ መጨረሻ ከህብረት ባንክ ጀርባ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አጠገብ ኢኢግልድ የማዕከላዊ ዲስትሪክት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች እና ውጤቶች ግዥ እና ሽያጭ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO ብቻ (ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን (financial) እና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች (technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በተመሳሳይ ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ስልክ ቁጥር:- +25114709554 ወይም +251114422509

 

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት

 

Save Tender