በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል እና በስሩ ላሉት ተቋማት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የፅዳት እቃ ግዥ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል እና በስሩ ላሉት ተቋማት ለ2018 በጀት ዓመት ለስራ የሚያገለግሉ የፅዳት እቃ ግዥ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ጨረታውን መወዳደር ለሚፈልጉ ተሳታፊዎች የጨረታ መስፈርት
- በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TON NO) ያለው
- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ወይም CPO ወይም በጥሬ ማስያዝ ይኖርበታል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸው ሠነድ ዋጋ በመሙላት በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ22ኛው ቀን በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 300.00 ብር (ሶስት መቶ ብር) ከተማ ስራ አስኪያጅ ፋይናንስ ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በከተማ ስራ አስኪያጅ ፋይናንስ ግ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል።
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ በአቅራቢነት መሞላት ያለበት ተሞልቶ የተጫራች ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ የስ/ቁ. 09 27 80 34 67 ወይም 09 15 75 53 24
አድራሻ፡- ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ (ቴሌ ትራፊክ መብራት አጠገብ)
ድሬዳዋ ከተማ ሥራ አስኪያጅ ጽ/ቤት
