Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1-ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፤ ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ፤ ሎት 3-የኮምፒውተር መሳሪያዎች፤ ሎት 4- የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፤ ሎት 5- ፈርኒቸር፤ ሎት 6- የፅዳት እቃ፤ ሎት 7- የውሃ እቃ፤ ሎት 8- የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፤ ሎት 9- የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ እቃ፤ ሎት 10- የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ሎት 11- የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና አሮጌ የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ሎት 1-ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፤ ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ፤ ሎት 3-የኮምፒውተር መሳሪያዎች፤ ሎት 4- የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች፤ ሎት 5- ፈርኒቸር፤ ሎት 6- የፅዳት እቃ፤ ሎት 7- የውሃ እቃ፤ ሎት 8- የኮንስትራክሽን ማቴሪያል፤ ሎት 9- የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ እቃ፤ ሎት 10- የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪም ሎት 11- የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችና አሮጌ የመኪና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከሎት 11 በስተቀር የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመነ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን፤ ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር እና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሰረዝ መደለዝ ከጨረታ ውድቅ የሚያደርግ መሆኑን አውቀው በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የእቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም መ/ቤቱ ባስቀመጠው ናሙና መሰረት መሞላት አለበት።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው 100 /መቶ ብር/ በመክፈል በመ/ቤታችን ረዳት ገ/ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 እና 14 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት1-ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች 9,500 /ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት 2 የፅህፈት መሳሪያ 12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ፤ ለሎት 3 የኮምፒውተር መሳሪያዎች 18,500 /አስራ ስምንት ሺህ አምስት መቶ ብር/፤ ለሎት 4 ኤሌክትሪክ እቃዎች 600 /ስድስት መቶ ብር/ ፤ለሎት 5 ፈርኒቸር 7,500 /ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት 6 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/፤ ለሎት7 የውሃ እቃ 22,000 /ሃያ ሁለት ሺህ ብር/ ፤ ለሎት 8 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል 12,500 /አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/፤ ለሎት 9 የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግ እቃ ለእያንዳንዳቸው መኪና /ተሽከርካሪ/ ሞዴል 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ ፤ ለሎት 10 የሚወገድ ብረታ ብረት 3,500 /ሶስት ሺህ አምስት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመ/ሂ 1 ማስያዝ አለባቸው።
  11. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናልና ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ 8:00 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 8:30 ይከፈታል ሆኖም ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን እና ካሉት አምስት የስራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  13. መ/ቤቱ በጨረታው በሚዝዙ ግዥዎች ላይ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
  15. ማንኛውም ተጫራቾች ግዥው በጥቅል (በሎት) የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ ፋስት ሙቪንግን በተመለከተ አሸናፊ የሚለየው በእያንዳንዱ መኪና ሞዴል ሲሆን የተዘረዘሩት እቃዎች በሙሉ ጠቅላላ ለእያንዳንዳቸው ዋጋ ያለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል። እንዲሁም አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ሳያጠናቅቁ ክፍያ የማይፈጸም መሆኑን እና በውለታው መሰረት እቃውን ጨርሰው ለመ/ቤቱ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው። ሎት 11 የሚወገዱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን እና አሮጌ የመኪና እቃ መለዋወጫ ሽያጭን በተመለከተ ከላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች መካከል የጨረታ ማስከበሪያ በማሲያዝና የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ብቻ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-226-01-64 ወይም 033-226-01-44 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

በደቡብ ወሎ ዞን የጃማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

Save Tender