Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ADDIS ABABA HOUSING DEVELOPMENT CORPORATION (የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን፡-

 

  1. በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ማ/ጨ/003/2018 በሎት-1 የመኪና ጎማ፣ ባትሪና ጌጣጌጥ ግዥ በሎት2.  የቢሮ አላቂ የፅህፈት መሣሪያ፣ ካሜራ፣ አምፒሊፋየርና ተዛማጅ ዕቃዎች፤
  2. በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/004/2018 የህንፃ ጥገና እና ዕድሳት አገልግሎት፤
  3. በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/005/2018 የቢሮ መሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የ2017/2018 የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ እና ንግድ ምዝገባ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ ገፅ /Online/ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማስረጃቸውን ኮፒና ኦርጅናል አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለው ህንፃ ላይ 4ኛ ፎቅ በኮርፖሬሽኑ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/003/2018 ለሎት-1፣ ለሎት 2 እንዲሁም ለግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ማ/ጨ/005/2018 የቢሮ መሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ ለእያንዳንዳቸው ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም ለግልፅ ጨረታ ቁጥር ቤ/ል/ኮ/ግ/ጨ/004/2018 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው፡-

  1. የመሬት ምንጣፍ እና መጋረጃ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም
  2. የመኪና ጎማ ባትሪና ጌጣጌጥ ግዥ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም
  3. የቢሮ አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች ግዥ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም
  4. የህንፃ ጥገና እና ዕድሳት አገልግሎት ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ 9ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 901 ይከፈታል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ባንቢስ አካባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የቤቶች ልማት ሕንፃ

ስልክ ቁጥር:- 0936 99 35 20/0911 36 97 83

 

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

 

Save Tender