Tender Detail

Tender Details


የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነገሮች ለ2018 የበጀት አመት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች ለ2018 የበጀት አመት 1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ለመፈፀም በሥራ ላይ የሚውሉ የተለያዩ

ሎት 1. 6211 ደንብ ልብስ ............................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 78,444.06

ሎት 2. 6212 የጽህፈት መሳሪያ ........................ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 107,303.34       

ሎት 3. 6213 ህትመት ስራዎች ......................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00                     

ሎት 4. 6218 የጽዳት እቃዎች .......................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 80,000.00         

ሎት 5. 6219 ልዩ ልዩ መሳሪያ .......................... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00         

ሎት 6. 6232 ትራንስፖርት ............................. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00         

ሎት 7. 6241 የተሸከርካሪ መኪና አልባሳት፣ ጎማ እና የሞተር ሳይክል ጎማ .......... የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00           

ሎት 8. 6313 ቋሚ እቃ ........................ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000.00                                

በዚሁም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ፡-

  1. በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደረያ ሃሳብ የዕቃውን አይነት፤ ስም የተመረተበት ሀገር የሞዴሉን ቁጥር የተመረተበትን ጊዜ ያካተተ መሆን ይገባዋል።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው በተጨማሪ የጨረታ ሰነድ ገንጥሎ ማስቀረት የተከለከለ ነው።
  4. ተጫራቾች የእቃውን ናሙና ከየዓይነቱ አንዳንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ ያቀረቡት ናሙናዎች በተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊዎቹ ተጫራቾች ናሙና ግን አይመለስም።
  5. ግዥ ፈጻሚው አካል ለአሸናፊ ተጫራቾች በሚመረጡበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልገሎት መጠን እንደ አስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
  6. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ጨረታው ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  7. የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በገንዘብ ተወስኖ በየሎቱ በተጠቀሰው መሰረት ሲፒኦ /CPO/ በኢቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል በማሰራት በዋናው ወይም በኦርጅናል ሰነድ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተም በሠነዱ ላይ በመምታት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖለታ በማድረግ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድነት በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ ጨረታ ለማገልገል በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።
  9. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ በሚጫረቱት የጨረታ ዋጋ ላይ በመመስረት የሚመለስ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ዝርዝር ጉዳዩን የያዘ ሰነድ ከጽ/ቤቱ መግዛት ይኖርባቸዋል።
  11. ተጫራቾች የአይሲቲ /ICT/ ዕቃዎችንና ሌሎች ቋሚ ዕቃዎችን ካሸነፉ ለ2 ዓመታት ዋስትና መግባት አለባቸው።
  12. የጨረታው ሳጥን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 04:00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ሠአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
  13. ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09-10-76-03-79/09-47-38-58-72/09-11-57-23-59/09-17-04-21-86
  14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ተጫራቾቸ የመወዳደሪያ ሳምፕል ጨረታ ከመዘጋቱ ከ2 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና/ሳምፕል ላይ ምንም አይነት ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶችን ማድረግ ከውድድር ውጪ ያደርጋል።
  16. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት እቃ ላይ የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከሚያመርቱት እቃ ውጪ ከሆነ በደብዳቤው መስተናገድ አይችሉም።

 

አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ወደ ደብረ ዘይት በሚወስደው መንገድ ከቤተሰብ መምሪያ አጠገብ ነው።

 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender