በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው ዕቃዎች ለመግዛት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ፦ 001/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸው የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 2 የሠራተኞች የደንብ ልብስ ሎት 3 የመኪና ጎማ ሎት 4 የስፖርት ትጥቅ ሎት 5 የተሽከረካሪ መለዋወጫ እቃዎች ሎት 6 የተሽከረካሪ መለዋወጫ እቃዎች ሎት 7 ፈርኒቸር እቃዎችና የፈርኒቸር ውጤቶች ሎት 8 የጽዳት እቃዎች እና ሎት 9 የህንጻ መሳሪያ እቃዎች ሎት 10 የመኪና ሞተር ዘይት ሎት 11 የውሃ እቃ ሎት 12 አቅርቦቶችን ለመግዛት በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- ከሚወዳደሩት ሥራ ጋር የተዛመደ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
- የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት (tax payer identification number) ያላቸው
- የግዥው መጠን ከ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ value added tax certificate) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት።
- የሚገዙ እቃዎች እና የግንባታ ሥራ አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሎት ምድብ/ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል አበ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ፋይናንስ ቡድን ዋና ገንዘብ ያዥ ላይ የጨረታው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንኮች በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን ገቢ ደረሰኝ የሚያሲዙ ከሆነ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነድ ጋር ታሽጎ ተያይዞ መቅረብ አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ እስከ ተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። በ16ኛው ቀን የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ በአበረገሌ ገንዘብ ግ/ን/አስ/ር/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3፡00 በማስገባት ከጠዋቱ 3፡31 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በአስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡31 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፣ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን አለበት እና የጨረታ ሰነዱ በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ወጥ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየ ብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት ኦርጅናል ብቻ አቅርበው በጨረታው ላይ ቅሬታ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት ዋጋ ሲሞሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ስፔስፌክሽን መሰረት ዋጋ መሞላት አለበት ነገር ግን በራሱ ስፔስፌክሽን ዋጋ የሞላ ተቀባይነት አይኖረውም ከውድድር ወጪ ይሆናል። እንዲሁም የተሞላ ዋጋ ቫት የተጨመረ መሆኑን መገለጽ አለበት ካልሆነ ቫት እንደተካተተ ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል።
- ተጫራቾች ደንብ ልብስ በእያንዳንዱ ዋጋ ሲሞሉ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ስፔስፌክሽን መሰረት ዋጋ መሞላት አለበት። ጨረታ አሸናፊ መ/ቤቱ ባቀረበው /በመረጠው/ ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አበርገሌ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር/ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 0912473621 ወይም 0923439250 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች ለመወዳደር ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ሃላፊነት የማይወስድ ወይም ወጪውን የማይሸፍን መሆኑን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በየጊዜው ማሻሻያ በማድረግ በወጡ ህጎች ተግባራዊ ይሆናሉ።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት በአሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ የሚችል መሆኑን ማወቅ አለበት እንዲሁም የጨረታ አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ከ5 የቅሬታ መስሚያ ቀናት በኋላ ባሉ 5 የሥራ ቀናት የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መወሰድ አለበት።
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ የአበረገሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
