Tender Detail

Tender Details


የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ እና እና ልዩ ልዩ በሀራጅ አና በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የግልፅ እና የሀራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት ዕቃ፣ ምግብ እና እና ልዩ ልዩ በሀራጅ አና በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 04/02/2018 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈለጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሀራጅ ጨረታው 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚቸል፤
  3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሀራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባለ፤
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃ ክፍያውን በ5 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሰ.ፒ.ኦ (C.P.O) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያላሽነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ሶ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይቸላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሽነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ በማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፣
  11. ተጫራቹ ለቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 04/02/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ት/ ጽ/ቤት የዕቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ06/01/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  13. የሀራጅ ጨረታው የሚካሄደው 06/02/2018 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B:-

አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡

 

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender