በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 1/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የሚከተሉትን የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር 1/2018 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የሠራተኛ የደንብ ልብሶች ................... ሎት 1 .............. የበጀት ኮድ .............. 6211
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች .......................... ሎት 2 ................ የበጀት ኮድ ............ 6212
- አላቂ የህክምና ዕቃዎች ...................... ሎት 3 .............. የበጀት ኮድ .............. 6214
- የትምህርት እቃዎች .......................... ሎት 4 .............. የበጀት ኮድ .............. 6215
- ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች አቅርቦቶች .......... ሎት 5 ......... የበጀት ኮድ .......... 6218
- ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ...................... ሎት 6 ................. የበጀት ኮድ .............. 6219
- ቋሚ ዕቃዎች .............................. ሎት 7 ................. የበጀት ኮድ ............... 6313
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-
- በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 07 ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ የማይመለስ በመክፈል የጨረታውን ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሠነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11፡00 ሰዓት ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የሥራ ሠዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይንም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው ሠነድ ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የተወዳሩበትን ጠቅላላ ዋጋ በየሎቱ ብር 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ላላሸነፉ ተጫራቶች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያው ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙን ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች በራሱ (በተጫራቹ) ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረስባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በስተቀኝ በኩል ባለው ደብረ ዘይት መንገድ አዲስ የተሰራው ድልድይ ላይ 200 ሜ ወደ ግራ ታጥፎ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-11-93-95-47/ 09-11-74-51-13 ደውለው ይጠይቁ፡፡
ፊታውራሪ አባይነህ መተኪያ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
