ሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Sebeta Special Need Education Teacher's College (የሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
ሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች፣ ሎት 2. የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምተሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎቶች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከኮሌጁ ሂሳብና በጀት ቢሮ ቁጥር 128 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ ሰበታ የልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት CPO በጀርባው የባንኩን መሃተም እና ስልክ ቁጥር ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ (15%) በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስፈር አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ በመጋዘን ቀድመው ማከማቸት ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ የሎት አንድ (1) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰዉ ቀን 4:30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-3-38-36-38/09-25-58-63-38/
ሰበታ ልዩ ፍላጎት ትምህርት መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ
