በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 የመኪና ዘይት፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 7 የቢሮ እቃዎች/ፈርኒቸር፣ ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 9 በሬድ ፕላስ ፕሮጀከት ፖሊታቲዩብ/ የችግኝ ፕላስቲክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአብክመ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት አመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 4 የመኪና ጎማ፣ ሎት 5 የመኪና ዘይት፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 7 የቢሮ እቃዎች/ፈርኒቸር፣ ሎት 8 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 9 በሬድ ፕላስ ፕሮጀከት ፖሊታቲዩብ/ የችግኝ ፕላስቲክ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
1, በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2.የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN) ነበር ያላቸው፤
3.ዮግዥ መጠን ጥቅል ዋጋ ከ200,000 በላይ (ከሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል .
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5.የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሻትን ጨምሮ በሰንጠረዡ በተገለጸው መሰረት
|
ለሎት 1 |
ለሎት2 |
ለሎት3 |
ለሎት4 |
ለሎት5 |
ለሎት6 |
ለሎት7 |
ለሎት8 |
ለሎት9 |
|
45,000 ብር
|
2,000ብር |
9,000ብር |
40,000ብር |
34,000ብር
|
15,000ብር |
7,000ብር |
40,000ብር |
10,000ብር |
በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገ/ያዥ ገቢ በማድረግና ገቢ ያደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ/ስፔስሬፊኬሽን /ከጨረታ ሰነድ ማግኝት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ( አራት ሰዓት ) ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡
10. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው !
12. ጨረታው ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
13 በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-4-61-03-35 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአብክመ በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የደሀና
ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
አምደወርቅ
