Tender Detail

Tender Details

  • Company Hawassa University College of Agriculture (ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462204740
  • Website
  • Deadline14 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price150.00
  • Bid Security5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-10-14 00:00:00
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ ለቢዝነስ ማዕከል ያስገነባውን ህንጻ ለተለያዩ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

Hawassa University College of Agriculture (ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ)


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የቤት ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር HUCA/NCB/RENT 2/2018 BY

 

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ ለቢዝነስ ማዕከል ያስገነባውን ህንጻ ለተለያዩ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000013552464 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ የውስጥ ገቢ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ግብርና ኮሌጅ ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ለሚፈልጉት የንግድ ዘርፍ የዘመኑን እድሳት የተከናወነበት በዘርፉ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡበትን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ለተለያዩ ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን /ሲፒኦ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /5,000.00/ አምስት ሺህ ብር በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ስም ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ክፍል ከፍለው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ደረሰኙን ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ጨረታው ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ጥቅምት 04 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ ግቢ በሚገኘው ግዥ አስተዳደር የስራ ሂደት ቡድን ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የተጫረቱበትን ክፍሎች ለፈለጉት የንግድ ዘርፍ በመጥቀስ በጨረታ ሰነዱ መሙላትና ወርሀዊ ክፍያውን ቢያንስ በ3 ወር አንዴ ቀደም ተብሎ መክፈል የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  7. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0462204740 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
  8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ

 

Save Tender