የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የንፅህና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸርና ጎማ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የንፅህና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸርና ጎማ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡-
- ተጫራቾች ህዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2018 ዓ.ም ፍቃድ ያሳደሱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በዕቃ አቅራብዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በግልጽ የምታዩ ህጋዊ ማስረጃዎችንና ከሚመለከታቸው የምስክር ወረቀቶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው መካፈል ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም የተግለጹትን ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተከበረ ነው።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ስህተት ቢፈጸም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል፡፡
- ለጨረታ የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ መጻፍ አለበት፡፡
- የጨረታው ሰነድ financial document እና technical document በዬ ፖስታ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታው ሳጥን ማስታውቂያው ከወጣበት ከ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ከ 27/01/2018 እስከ 17/02/2018ዓ.ም ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በሳምፕል የምቀርቡ ዕቃዎች፣ ትልቅ አጀንዳ፣ መካከለኛ አጀንዳ፣ ደንብ ልብስ በዳለቻ መልክ እና የእስቴፕለር መርፌ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡
- መስሪያ ቤቱ ከአጠቃላይ ግዥ 2% ዊዝሆልዲንግ ታክስ (with holding tax) እና 7.5% ቫሊዩ አድድ ታክስ (value added tax) የሚቆርጥ መሆኑን አቅራቢው ድርጅት ማወቅ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሰነዱ አይነት 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር ቴክኒክ ፖስታ ውስጥ ማስቀመጥ አለበት፡፡
- አሸናፊ ከሆኑ ተጫራቾች ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይገባሉ፡፡ እንዲሁም አሸናፊው ውል በሚገቡባቸው ዕቃዎች አጠቃላይ ዋጋ ውል ማስከበሪያ 2% ያስዛሉ የተዋዋሉበት ንብረትም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የዘዙበትን አሪጅናል ሪስት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነድ በየሰነዱ አይነት በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ከአሙሩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ የገዛቸውን ዕቃዎች የሚረከበው በአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ወረዳችን የሚትገኘው በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሲሆን ከአዲስ አበባ እስከ ሻምቡ አስፋልት 322 ኪሎ ሜትር ከሻምቡ እስከ አሙሩ 72 ኪሎ ሜትር ፒስታ በአጠቃላይ 394 ኪሎ ሜትር ላይ ይገኛል፡፡
አድራሻችን፡- አሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አበራ
ተጨማሪ መረጃ ለማገኘት በ 0917078125 ወይም 0900590448 ላይ ደውለው መረዳት ይቻላል፡፡
የአሙሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
