በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግዥዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ግዥዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
ሎት 1 - አላቂ የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2 - የተሽከርካሪ ኦሪጅናል መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 3 -ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 4 - የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች እና ሎት 5 - ፈርኒቸር
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች እንዲወዳደሩ ይጋብዛሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመወዳደር የሚያስችል በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የስራ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑትን የምዝገባ ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ለሁሉም ሎቶች፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1- አላቂ የጽ/መሳሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ሎት 2 የተሽከርካሪ ኦሪጅናል መለዋወጫ እቃዎች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ሎት 3 - ኤሌክትሮኒክስ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ፣ ሎት 4 – የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ሎት 5 -ፈርኒቸር ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ፣ በጥሬ ገንዘብና በሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ለብቻው በማሸግ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሎት 2 - የተሽከርካሪ ኦሪጅናል መለዋወጫ እቃዎች እና ሎት 1 - አላቂ የጽ/መሳሪያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሰነዱን ዋናውና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በሁለት ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በሸኮ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ይህ ጨረታ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ዕቃዎችን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው እስከ ወረዳ ማእከል ማቅረብ እና ፈርኒቸሩ በራሳቸው ወጪ እና ባለሙያ መግጠም የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
አድራሻ፡- ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማ/ጽ/ቤት
ስልክ ቁጥር- 047-7-78-02-61
በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ የቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
