ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር በሸገር ከተማ አስተዳደር ወለቴ አካባቢ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ህንፃ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።
MIDROC GOLD Mine P.L.C (ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር)
የህንፃ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር በሸገር ከተማ አስተዳደር ወለቴ አካባቢ የሚገኘውን ዘርፈ ብዙ ህንፃ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉትን ተጫራቾች እንደሚከተለው ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በሸገር ከተማ አስተዳደር ወለቴ አካባቢ የሚገኝውን ዘርፍ ብዙ ህንፃ በአካል ተገኝቶ በማየት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ለጨረታ መስከበሪያ ህንፃውን የሚከራዩበትን ዋጋ 2% በማስያዝ፣ ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት መመዝገብ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ከፍለው በመውሰድ የጨረታ ሰነዱ ላይ ሊከራዩ የሚፈልጉትን ህንፃ ቁጥር በመጥቀስ የሚከራዩበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊትና በኋላ በግልፅ በመጥቀስ የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሠዓት ጠዋት ከ3፡00 ሠዓት እስከ 6፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዕለቱ አርብ ጥቅምት 07 ቀን 2018 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ በ8፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የማይችል ሲሆን ነገር ግን አንድ ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ በመግዛት ከአንድ ክፍል በላይ መጫረት ይችላል።
- በጨረታው ለተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ሲመለስላቸው ለአሸናፊዎች ግን ከኪራዩ ክፍያ ታሳቢ የሚደረግ ይሆናል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን የህንፃ ኪራይ ዋጋ ከፍለው በሰባት (7) የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን ውል መፈፀም አለባቸው። ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙትን ገንዘብ /ሲ.ፒ.ኦ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሠረዛል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ሰሚት ፋርማኪዩር በሚገኘው ግቢ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር የቢሮ ማግኘት ይችላሉ::
ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0921-10-12-47 እና 0917-83-32-06 ይጠቀሙ።
አድራሻችን ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሰሚት
ፋርማኪዩር ግቢ ውስጥ እንገኛለን።
