Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአፈፃፀም ብቃት ላይ ተመስርቶ በሚቆይ የአንድ ዓመት የኮንትራት ውል እና የተወሰኑትን ዕቃዎች /አገልግሎቶች ለአንድ ጊዜ ብቻ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa Culture and Arts Bureau (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር- አ/አ/ባ/ኪ/ቢ/001/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነጥበብ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በዘርፉ የተሰማሩ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአፈፃፀም ብቃት ላይ ተመስርቶ በሚቆይ የአንድ ዓመት የኮንትራት ውል እና የተወሰኑትን ዕቃዎች /አገልግሎቶች ለአንድ ጊዜ ብቻ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታክስ ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወቀረት፣ ተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፣

የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ እና 6 ወር ያልበለጠው ወቅታዊ በጨረታ ለመሳተፍ እንድችሉ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የጨረታ ተሳትፎ ፈቃድ /TAX CLEARANCE/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከተውን በሚወዳደሩበት እያንዳንዱ ሎት ፊት ለፊት የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ በዋናው የቴክኒከ ሰነዳቸው አካትተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት 2018 በጀት ዓመት የተፃፈ እና በጽ/ቤት ኃላፊ የተረጋገጠ የድጋፍ ደብዳቢ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

 

  1. የኮንትራት ውል የሚፈፀሙ

 

ሎት

የዕቃው/የአገልግሎቱ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

 

በአንድ ጊዜ የውል አገልግሎት የሚፈፀም

5,000.00

ሎት1

የደንብ ልብስ

10,000.00

ሎት2

የቢሮ የፅዳት እቃዎች

1,000.00

ሎት3

የቢሮ የፅህፈት እቃዎች

1,000.00

ሎት4

ኮምፒውተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች

1,000.00

ሎት5

የመኪና ጎማ ፣ ባትሪና፣ ጌጣጌጥ

10,000.00

ሎት6

የሙዚቃ መሳሪያ

25,000.00

ሎት7

የልቦለዳዊ ፊልም

15,000.00

 

በዓመታዊ የውል አገልግሎት የሚፈፀም

 

ሎት8

ከከተማ ውጭ ትራንስፖርት አገልግሎት

10,000.00

ሎት9

የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት

10,000.00

ሎት10

የመኪና ሰርቪስ አገልግሎት

10,000.00

ሎት11

የተለያዩ ድንኳኖች

10,000.00

ሎት12

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና

10,000.00

ሎት13

የሬዲዮ የአየር ሰዓት እና ፕሮዳክሽን

15,000.00

ሎት14

የቴሌቪዥን የአየር ሰዓት፣ ፕሮዳክሽን እና ቶክ ሾው

30,000.00

ሎት15

ሲትኮም ዱራማ

25,000.00

ሎት16

መላከለኛ መድረክ

10,000.00

ሎት17

ዲኮር

5,000.00

ሎት18

የተለያዩ ህትመቶች

------------

ሎት18.1

መጽሔት

1,000

ሎት18.2

ጋዜጣ /የዕደጥበብና ባህል እሴቶች/

8,000.00

ሎት18.3

ብሮሸር

5,000.00

ሎት18.4

ሰርተፊኬት /የምስክር ወረቀት/በ MDF/

10,000.00

ሎት18.5

ባነር

8,000.00

ሎት18.6

ሮልአፕ ባነር

8,000.00

ሎት18.7

ዌብሳይት መጠቆሚያ ካርድ

5,000.00

ሎት18.8

የደረት ባጅ

5,000.00

ሎት18.9

ፖስተር

7,000.00

ሎት18.10

ስቲከር

5,000.00

ሎት18.11

መታወቂያ

10,000.00

ሎት18.12

ካታሎግ ህትመት

15,000.00

ሎት18.13

ጆርናል ህትመት

15,000.00

 

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ፍላሚንጎ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ (8ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 804/805) በመክፈል ከ7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ (7ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 701) ሰነዱን በሶፍት ኮፒ፤ በኢሜል ወይም በፍላሽ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመግዛት እስከ 11ኛው /አስራ አንደኛው/ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ የሰነዱን ዋና በኢንቬሎፕ እንዲሁም ቅጂ በኤንቨሎፕ በማሸግ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ (7ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 701) ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው (አስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 701 ይከፈታል፡፡11ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተያዘለት ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች እንደ ጨረታው ባህሪ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው አገልግሎቶችና ዕቃዎች ተገቢውን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እያንዳንዱን ዕቃ አገልግሎት የመጫረቻ ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር መግለጫ /Specification/ እና መለኪያ መሠረት ቫትን ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እንደ ጨረታው ባህሪ/ቴክኒካል መስፈርተር ላለው ለእያንዳንዱ ሎት እንዳስፈላጊነቱ የቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሠነድ ዋና እና ቅጂ በማዘጋጀት በእያንዳንዱ ኤንቨሎፕ የሎቱን ዋና እና ቅጂ በግልጽ በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች በተ.ቀ.1. የተዘረዘሩትንና ሌሎች በጨረታ ሠነዱ ውስጥ የተገለጹ አስፈላጊ መረጃዎችን ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር: 011-126 45 86 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

 

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳደር ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ

 

Save Tender