Tender Detail

Tender Details

  • Company ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address ባህር ዳር አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0583218865
  • Website
  • Deadline13 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-13 00:00:00
  • Categories Printed Advertising Materials , Printing And Publishing , Used Items , Byproducts

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ የተለያዩ የሕትመት ተረፈ ምርቶች ባሉበት ሁኔታ ለአንድ አመት የሚቆይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር አሕየወፓ-ሽ 01/2018

 

ዓባይ የህትመትና የወረቀት ፓኬጅንግ ፋብሪካ የተለያዩ የሕትመት ተረፈ ምርቶች ማለትም (80 ግራም ህትመት የተሞከረበት ወረቀት፣ ፕሌት ከነ ቁርጥራጩ፣ 80 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ 60 እና 45 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ ኮር (የወረቀት መጠቅለያና የላምኔሽን ፊልም መጠቅለያ ጨምሮ) በተለያየ መጠን የተቆራረጠ ላምኔሽን፣ 60፣ 80 አና 45 ግራም ቁርጥራጭ ወረቀት፣ የመጽሀፍ ከቨር፣ እና መጽሀፍ፣ ፓስ ቡኮች፣ የፕላስቲክ ገመድ፣ ሪል ወረቀት የሚሸፈንበት ግልፋፊ ወረቀት፣ ሪል ወረቀት ከስር ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካርቶን፣ አርት ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካኪ/ወረቀት፣ የኮር ቀለበት፣ የመጽሀፍ መስፊያ ሽቦ ተጠቅልሎ የሚመጣበት የሽቦ መጠቅለያ፣ ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት የተለያየ አይነት እና መጠን ያላቸው ፕላስቲክ /ፌስታል፣ ባለ 5ሊትር ጀሪካን፣ ባለ 3ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለው ባለ 3ሊትር ጀሪካን፣  ክዳን የሌለው ባለ 5ሊትር ጀሪካን፣ የተለያዩ መጠን ያለው ያገለገለ ብላንኬት፣ የተለያዩ መጠን ያለው ያላገለገሉ /ን/ህ/ ብላንኬት፣ ብላንኬት ታሽጎ የመጣበት የካርቶን ቱቦ፣ 200ሊትር የአልኮል የጎማ በርሜል፣ ባለ 15 ሊትር የቀለም ጣሳ፣ ባስ 2 ሊትር የቀለም ጣሳ፣ ባለ 20ኪሎ እና 25 ኪሎ የሚይዝ የሆትሜል ግሉ ኮላ ቀረጢት እና ፕሌት ክሊነር የመጣበት ባለ 1ሊትር ጎማ ባሉበት ሁኔታ ለአንድ አመት የሚቆይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሰረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

  1. ማንኛውም ድርጅት፣ ተቋም ወይም አሸናፊው ግለሰብ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና (TIN) ያላቸው መሳተፍ ይችላሉ፣
  2. የወረቀት ተረፈ ምርቱ የሚገኝበት ቦታ ማየት የፈለጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታዉ መዝጊያ ቀን ድረስ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከፋብሪካዉ ግቢ ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ኢንዱስትሪ መንደር ከሚገኘዉ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ስዓት በማምጣት እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይቻላሉ፤
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሰነዱ ጋር ማቅረብ አሰባቸው። አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ የውል ማስከበሪያ 80 ግራም ህትመት የተሞከረበት ወረቀት፣ ፕሌት ከነ ቁርጥራጩ፣ 80 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ 60 እና 45 ግራም ግልፋፊ ወረቀት፣ ከዚህ በላይ ላሉት የውል ማስከበሪያ 50,000 ብር (ሃምሳ ሽህ ብር) ማስያዝ አለበት:: ባለ 15 ሊትር የቀለም ጣሳ እና በተለያየ መጠን የተቆራረጠ ላምኔሽን የውል ማስከበረያ 20,000 ብር (ሃያ ሺህ ብር) ሲሆን ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ማለትም የመጽሀፍ ከቨር፣ መጽሀፍ ፓስ ቡኮች፣ የፕላስቲክ ገመድ፣ ሪል ወረቀት ከስር ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካርቶን፣ የአርት ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት ካኪ/ወረቀት፣ የኮር ቀለበት የመጽሀፍ መስፊያ ሽቦ ተጠቅልሎ የሚመጣበት የሽቦ መጠቅለያ፣ ወረቀት ተጠቅልሎ የሚመጣበት የተለያየ አይነት እና መጠን ያላቸው ፕላስቲክ /ፌስታል፣ ባለ 5ሊትር ጀሪካን፣ ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለው ባለ 3 ሊትር ጀሪካን፣ ክዳን የሌለው ባለ 5ሊትር ጀሪካን፣ የተለያዮ መጠን ያለው ያገለገለ ብላንኬት፣ የተለያዩ መጠን ያለው ያላገለገሉ /ን/ህ/ ብላንኬት፣ ብላንሌት ታሽጎ የመጣበት የካርቶን ቱቦ፣ ባለ 200 ሊትር የአልኮል የጎማ በርሚል፣ ባለ 2 ሊትር የቀለም ጣሳ ባለ 20ኪሎ እና 25 ኪሎ የሚይዝ ሆትሜል ግሉሱ የኮላ፣ የፕሌት ክሊነር የመጣበት ባለ 1ሊትር ጎማ እና የወረቀት መጠቅለያና የላምኔሽን መጠቅለያ ጨምሮ ለእያንዳንዱ 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር) ማስያዝ አለባቸዉ።
  5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በቅንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፋብሪካ ገዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ቢሮ ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። በመሆኑም ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  7. ፋብሪካዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ሲያስፈልግ ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ግዥና ሎጅስቲክስ መምሪያ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583218865 በመደወል ማግኘት ይቻላል፤

 

ዓባይ ሕትመትና የወረቀት ፓኬጂንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ባህር ዳር

 

Save Tender