የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በተቋሙ ተጠቃሚ ለሆኑ ዲፓርትመንቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በ11 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በተቋሙ ተጠቃሚ ለሆኑ ዲፓርትመንቶች የእቃና አገልግሎት ግዥዎችን በ11 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት1 የፅዳት እቃዎች
- ሎት2 የጽህፈት እቃ
- ሎት3 የደንብ ልብስ
- ሎት4 አላቂ እቃዎች
- ሎት5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት6 ፈርኒቸር
- ሎት7 የህንፃ ጥገና እቃዎች
- ሎት8 ህትመት ስራዎች
- ሎት9 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራ
- ሎት10 የጉልበት አገልግሎት
- ሎት11 የመኪና ኪራይ አገልግሎት
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፣ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን 5ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታ አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ካሸነፈባቸው ከእቃው ዋጋ 10% cpo በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት1 እስከ 11 ለእያንዳንዱ ሎት 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከተቋሙ ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ 5 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች ናሙና ማቅረብ የግዴታ ሲሆን ነገር ግን ከባድ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ከሰነዱ ጋር ካታሎግ ማስገባት ይኖርበታል ፣ ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉት ባመረታችሁት እቃ ብቻ ሲሆን አምራች መሆናችሁን የሚገልፅ ደብዳቤ በአደራጃችሁ ፅ/ቤት ሀላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡-
ኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ ካራ ቆሬ ወደ መድሐኒአለም ቤ/ክርስቲያን መውጫ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ በሚገኘው የጤና ጣቢያው ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 64
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጤና ጣቢያ
