በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ትምህርት ጽ/ቤት የሚገኘው ነፃነት ብርሃን ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ትምህርት ጽ/ቤት ነፃነት ብርሃን ቅድመ አንደኛ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የመጀመሪያ ዙር ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ትምህርት ጽ/ቤት የሚገኘው ነፃነት ብርሃን ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 የትምህርት ዘመን የሚያስፈልጉ ዕቃዎች፡ ማለትም
1. የደንብ ልብስ 2. የስፖርት ጫማ እና ትጥቅ 3. ፈርኒቸሮች 4. የፅዳት እቃዎች 5. አላቂ የቢሮ 6. ህትመት እና የኮምፒተርና የተለያዩ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ
- ለሚጫረቱበት እቃዎች በዘርፍ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው ፤ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች ኦርጂናሉን ከኮፒው ጋር በማመሳከር ኮፒውን ለብቻ አርጂናሉን ከጨረታ ሰነዱና ሲፒኦ ጋር በማያያዝ ማስገባት አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ /ቢድ ቦንድ/ የኢትዮጵያ ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ከፋይናንስ ቢሮ 03 የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላትና በማሽግ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃ ጨረታውን ሲያስገቡ ናሙና /ሳምፕል / አብረው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የአንዱ እቃ ዋጋ ሲያቀርቡ የቫትን ዋጋ ጨምረው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ይታሸግና በሚቀጥለው የስራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ከደንበል ሲቲ ሴንተር ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ድሪም ላይነር ሆቴል አጠገብ 35 ሜዳ ፊት ለፊት ነው።
ስልክ ቁጥር 0114-700371 ወይም 0114-166514
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 ትምህርት ጽ/ቤት ነፃነት ብርሃን ቅድመ አንደኛ፤አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
