Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ለዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ለዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የታደሰና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ባቅራቢያቸው ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው። አሸናፈው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አስከ ከፍተኛ ፍ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመስስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከላይ በተገለጸው የጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የመንግስት ስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደርያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገው እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 104 ገቢ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾቹ /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  9. በሽያጭ የቀረበው ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴው (አሸናፊው ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃውን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግደታ አለበት፡፡
  10. የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን ምዕ/ሐረርጌ ዞን ከፍታኛው ፍ/ቤት

ስልክ 0942015828

ሞባይል 0920454496

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት

 

Save Tender