Tender Detail

Tender Details


በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለቢሮ መገልገያ የሚሆን ሎት 1 ቋሚ እቃ፣ ሎት 2 የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 7 የህትመት ስራዎች፣ ሎት 8 መፅሀፍቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ለቢሮ መገልገያ የሚሆን ሎት 1 ቋሚ እቃ፣ ሎት 2 የህንጻ መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ፣ ሎት 4 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 5 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 6 የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ሎት 7 የህትመት ስራዎች፣ ሎት 8 መፅሀፍቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡

በግልፅ ጨረታው ለመወዳደር የሚያስፈልጉ መስፈርቶች-

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ያለው/ላት ፤
  2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ የሚያረጋግጥ በግብር ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበትን አይነት የማይመለስ ብር በየሎቱ ለአንድ ሎት/ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ፣
  5. ለእጅ በእጅ ደረሰኝ ለምትጠቀሙ ተጫራቾች ከገቢዎች እንድትጠቀሙ የተፈቀደበትን ደብዳቤ ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ማቅረብ የማይችሉ ተጫራቾች ተወዳድረው ቢያሸንፉ ክፍያ የማይፈፀም መሆኑን እንገልፃለን ፤
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት አይነት ለእያንዳዱ በሎት ቢድ ቦንድ /በሲፒኦ/ CPO / 5000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ / የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ማስያዝ ይኖረባቸዋል ፤
  7. ተጫራቾች የሚያቀረቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ፤
  8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በያንዳንዱ ሎት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየ ብቻ ታሽጎ ዘወትር በስራ ሰዓት እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤
  9. ተጫራቾች በምትጫረቱባቸው እቃዎች ላይ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ግዴታ ነው፣ በአካል መምጣት ለማይችሉ እቃዎችም ከሆኑ ደግሞ በፎቶ ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የጨረታው ጊዜ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፤ የመክፈቻው ቀን በአላትና የእረፍት ቀናት ላይ ከዋለ በሚቀጥሉት የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-93-20-89

 

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ጤና ጣቢያ

 

Save Tender