የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅራቢ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራ ማስጀመር ይፈልጋል፡፡
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ-ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅራቢ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ስራ ማስጀመር ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት አለባችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርቡ ፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ካፌና ሪስቶራንት ሆቴል፣ ምግብ ቤትና ባርና ሪስቶራንት እና ተመሳሳይ የሆነ ስራ ሊሰራ የሚችል ፡፡
- ተጫራቾች ቲኦቲ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ተከታታይ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ከመካነሠላም ሆስፒታል ዋና ገንዘብ ያዥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚከናወነው በሎት ሲሆን በመኖ ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበና በቤት ኪራይ መነሻ ዋጋ ብር 4000 ሲሆን ከዚህ በላይ ከፍተኛ ያቀረበ አሸናፊ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታው በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ 16 ኛው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታውን መክፈት ይቻላል፡፡
- የግብአት አገልግሎት ቢያንስ ለሶስት ወር በቂ የሚሆን በመጋዘን ማስቀመጥ የሚችል።
- የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ በፊት 2% በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢፈልግ 0923747044 0914344306፣0934370254 እና 0914334565 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የመካነ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል
