የመካነ ህይወት ቅድመ መደበኛ መካከለኛ አንደኛ ደረጃና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመካነ ህይወት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የመካነ ህይወት ቅድመ መደበኛ መካከለኛ አንደኛ ደረጃና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ
- አላቂ የቢሮ እቃዎችና ኬሜካሎች ሎት-1 6212-3000 ብር (ሦስት ሺህ ብር)
- አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች ሎት-2 6215-3000 ብር (ሦስት ሺህ ብር)
- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ሎት-3 6218 -3000 ብር (ሦስት ሺህ ብር)
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ ሎት-4 6211-4000 ብር (አራት ሺህ ብር)
- የህክምና እቃዎች
- ቋሚ እቃዎች ሲሆን ሎት-5 6313ና 6314 -4000 ብር (አራት ሺህ ብር)
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመካነ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተጨማሪ ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን አጠቃላይ ብር 17,000 (አስራ ሰባት ሺህ) ወይም የሚወዳደሩበትን ሎት በመምረጥ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ሲኖርባቸው ያሸነፉበትን ገንዘብ 10% በቼክም ሆነ በጥሬ ብር ለዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀን አየር ላይ ይውላል በ10ኛ ቀን በ10፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻችው) በተገኙበት ወይም ባይኖሩም በመካነ ህይወት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታው የማያዋጣው ሆኖ ካገኘው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- የመምህራን ጋወን እና የሰራተኛ ደንብ ልብስ የምታቀርቡት ናሙና ከ1 ሜትር መብለጥ የለበትም ም/ክ ት/ቤቱ በጥቅል የሚቀርቡ ናሙናዎች ሁሉን ኣሳታፊ ስላልሆኑ በናሙናነት አይቀበልም፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከ2 ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆን እንገልፃለን፡፡ ናሙና በማይቀርብባቸው እቃዎች ላይ በእስፔስፊኬሽናቸው መሰረት መቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ VAT ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን መስሪያ ቤቱ የቀረበው ዋጋ VATን እንዳካተተ ይቆጥራል፡፡ መረጃ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ማዞሪያ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ስልክ ቁጥር 011 1 14 00 12/ 011 154 93 41 ይደውሉ፡፡
የመካነ ህይወት ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
