በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪና የጀኔሬተር መለዋወጫዎች፣ የማሸነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኢፌዱሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መከ/ሰ/ምስ/ዕዝ/ግ/ጨ/01/2018
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪና የጀኔሬተር መለዋወጫዎች፣ የማሸነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ስነ - ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የተሟሉና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን በተራ ቁጥር 6 /ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ተ.ቁ 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ፋይናንሻልና ቴክኒካል እንዲሁም ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያና ሰነድ ማስገቢያ-
ሀ/ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ፡- ዘወትር በስራ ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሠመራ ከተማ የሰሜን ምስ/ዕዝ/ፋይ/ስራ/አመ/ዘርፍ ግዥ ክፍል ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0991454479/0939055793/
ለ/ የሰነዱ ሽያጭ የሚከናወንበት አድራሻ:- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡
ሐ/ ጨረታው የሚላክበት አድራሻ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡
መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ - በተቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ፡፡
ሠ/ ንብረቱ ገቢ የሚሆነው:- ሠመራ ከተማ ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ንብረት ግ/ቤት ነው::
ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
