የቶሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ 2018 ዓ/ም የሚያገለግሉ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ እላቂ እቃዎች (እስቴሽነሪ)፤ የጽዳት እቃዎች፤ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸር እቃዎች ለወረዳ ፍርድ ቤት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቶሌ ወረዳ ፍርድ ቤት
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የቶሌ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ 2018 ዓ/ም የሚያገለግሉ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ እላቂ እቃዎች (እስቴሽነሪ)፤ የጽዳት እቃዎች፤ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸር እቃዎች ለወረዳ ፍርድ ቤት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት የምችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀረብ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል።
- በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ኮፒው ና ኦርጅናሉን በማቅረብ ስም፣ ፊርማና አድራሻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ ከተገለፀው የዕቃ ፕሮፖዛል ውጭ ተመሳሳዩን ማቅርብ እንደ ማይቻልና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ በስህተት ቢቀርብ በሚፈለግበት ጊዜ መቀየር የሚችል፡፡
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 በቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ የከፍያ ማዘዣ (CPO) አምስት ሺ ብር (5000) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ በኋላ የውል ማስከበርያ ጠቅላላ ካሸነፈው ዕቃ የሚመለስ 10% ማስያዝ አለበት።
- ያሸነፈውን ዕቃ ናሙና መቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ ና ዕቃውን ጽ/ቤቱ ድረስ በራሳቸው ወጭ አምጥተው ካስረከቡ በኋላ ክፍያው ይፈፀማል።
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር (200) ሁለት መቶ ብር ከቶሌ ወረዳ ገቢዎች ከፍሎ ሠነድ ከቶሌ ወረዳ ፍ/ቤት መግዛት ይችላሉ።
- በ ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር (suppliers list) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ፎቶኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በ ከፊል ወይም ሙሉ በ ሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድረሻችን የቶሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፣ በሰበታ-አስጎሪ-ባንቱ መስመር ነው
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- 0113130004/0933355623/ 0913681954 መደወል ይችላሉ።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቶሌ ወረዳ ፍርድ ቤት
