የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የእንደኛው ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያ 1 ሎት2. ደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት 3 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣ሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣ ጌጣጌጥ እና ጥገና እቃዎች፣ ሎት 6 ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሣሪያ እድሳትና ጥገና ሰርቪስ፣ ሎት 7 ለቧንቧ እና ለኤሌክትሪክ ጠቅላላ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፣ ሎት 8 ቋሚ የኤሌከትሮኒከስ እቃዎችን፣ ሎት 9. ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች እና ሎት 10 ቋሚ የዲሞኒስትሬሽን (የህክምና) እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት የእንደኛው ዙር ግልፅ ጨረታ፣ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት መሣሪያ 1 ሎት2. ደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት ፣ሎት 3 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት 4 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ሎት 5. የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣ ጌጣጌጥ እና ጥገና እቃዎች፣ ሎት 6 ለፕላንት ማሽነሪ እና ለመሣሪያ እድሳትና ጥገና ሰርቪስ፣ ሎት 7 ለቧንቧ እና ለኤሌክትሪክ ጠቅላላ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች፣ ሎት 8 ቋሚ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎችን፣ ሎት 9. ቋሚ የፈርኒቸር እቃዎች እና ሎት 10 ቋሚ የዲሞኒስትሬሽን (የህክምና) እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ
- በመስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እና የግብር መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከወሰዱት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ውጪ በሌላ ሞልቶ ቢያቀርቡ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300 /ሶስት መቶ/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት እሰከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ11ኛው ቀን እስከ አራት ሰአት ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የሚከፈት ሲሆን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ከሎት1 ፤2፣3፣4፣5 ፣6 እና 7 ላለው ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ ሎት 9. 20,000 (ሃያ ሺ) የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ሲኖርባቸው እና ሎት 8 እና 10 50,000 ብር (ሃምሳ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ዘግይተው የቀረቡ የመወዳደሪያ ሠነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው ተወዳድሮ ያሸነፈውን እቃ በኮሌጁ ጥራት /ቴከኒክ/ ኮሚቴው ጥራቱ ሲረጋገጥ ተጫራቹ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ በኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ኮሌጁ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ወይም አገልግሎት ብዛት | መጠን እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20 በመቶ ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡
- የዳ/ም/ህ/ጤ/ሳ/ኮሌጅ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ በስልክ ቁጥር 0111-26-16-53 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ዳግማዊ ሚኒሊክ ኮምፕሬሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።
የዳግማዊ ምኒልክ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
