በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረዳ ቁጥር 1 ት/ቤት በጀት በ2018 ዓ.ም የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 007/2018 ዓ.ም
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረዳ ቁጥር 1 ት/ቤት በጀት በ2018 ዓ.ም የተዘረዘሩት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1. ልዩ ልዩ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የትምህርት ዕቃዎች
ሎት 2. ደንብ ልብስ
ሎት 3. የፅዳት እቃዎች
ሎት 4. ቋሚ እቃዎች
ሎት 5. ጥገና
ሎት 6. ህትመት
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች /ድርጅቶች/
ከዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እድትሳተፉ ተጋብዘዋል፤
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የአቅራቢዎች ምዝገባ እና የምስክር ወረቀት ያላችሁ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ለመጫረት የሚያበቃ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 6:30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11:30 የስራ ቀናት ውስጥ በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ግዥ ክፍል መመዝገብ ትችላላችሁ፤
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ትችላለችሁ ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ ሲፒኦ /በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ት/ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደራጃ እና መካከለኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት ስም ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ሎት 1. 8,000 ብር 2. ሎት. 8,000 ብር ሎት 5. 6,000 ሎት 3. 5,000 ብር ሎት4. 6,000 ብር ሎት 6. 4,000
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቦታ ይከፈታል ነገርግን የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዕቃዎች በሙሉ ጨረታውን ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አላባቸው፤
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተነስቶ ማቅረብ አይችልም፤
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ መሙላት አለባቸው፤
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
- አሸናፊው ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቀባቸዋል።
- ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6:00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት 7:30 እስከ 9:00 ድረስ መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፤
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁበት መስሪያ ቤት ደብዳቤ ይዘው ሲቀርቡ የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ ይችላሉ፤
- መ/ቤቱ የሚጫረታቸውን እቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20 ፐርሰንት ጨምሮ ወይም ቀንሶ ማዘዝ ይችላል፤
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ ተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የለውም፤
አድራሻ፡- ጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
ከቤቴል አዲስ ተስፋ ት/ቤት ፊት ለፊት
ከቤቴል አዳባበይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሚወስደው መንገድ ላይ ወደ ውስጥ ገባ ብለው
- የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ 0113697043 0921210112 0909249393
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ቁጥር 1 ት/ቤት
