የመድኃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብሶች እና የልብስ ስፌቶች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ህትመቶች፤ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ መስጫ መድኃኒቶች፣ የት/ት ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የእጅ መሣሪያዎች፣ ትራንስፖርት፣ የጉልበት ሰራተኛ፣ የማሽነሪ ጥገና እና የጥገና ዕቃ እና የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የመድኃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
የመድኃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት እና በውስጥ ገቢ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብሶች እና የልብስ ስፌቶች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ህትመቶች፤ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ መስጫ መድኃኒቶች፣ የት/ት ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣ የእጅ መሣሪያዎች፣ ትራንስፖርት፣ የጉልበት ሰራተኛ፣ የማሽነሪ ጥገና እና የጥገና ዕቃ እና የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ማለትም፡-
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር |
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር |
|
1 |
የደንብ ልብስ /621/ |
ሎት 1 |
16,000.00 |
7 |
የእጅ መሣሪያዎች /6219/ |
ሎት 7 |
1,000.00 |
|
2 |
አላቂ የጽ/መሣሪያ /6212/ |
ሎት 2 |
7,014.00 |
8 |
ትራንስፖርት /6232/ |
ሎት 8 |
600.00 |
|
3 |
ለህትመት /6213/ |
ሎት 3 |
800.00 |
9 |
የቀን ጉልበት ሰራተኛ |
ሎት 9 |
300.00 |
|
4 |
ለመጀመሪያ ህክምና እርዳታ /6214/ |
ሎት 4 |
500.00 |
10 |
የማሽነሪ ጥገና /6243/ |
ሎት 10 |
200.00 |
|
5 |
የት/ት ዕቃዎች /6215/ |
ሎት 5 |
6,000.00 |
11 |
የጥገና ዕቃ እና ስራዎች /6244/ |
ሎት 11 |
3,500.00 |
|
6 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች /6218/ |
ሎት 6 |
15,000.00 |
12 |
የመስተንግዶና የክበብ ኪራይ |
ሎት 12 |
20,080.00 |
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርቶች መሰረት ቀርባችሁ መወዳደር ትችላላችሁ።
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ከብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሚወዳሩ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ በሎት ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ስፔሲፊኬሽን የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ስፔሲፊኬሽን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዕቃ እና የአገልግሎት ግዥ ዋጋዎች የሚያቀርበው VATን ጨምሮ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ሳንፕል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀን ሆኖ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመድኃኔዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው አምራች እና እሴት የጨመሩ ከሆነ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና እና መቀነስ ይችላል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን የዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በሲፒአ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ጉ/ክ/ከተማ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ከመድኃኒዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጀርባ በስተቀኝ በኩል በግምት100 ሜትር ገባ ብሎ ወደ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን መውጫ መንገድ
ስልክ ቁጥር፡- 0112737627
የመድኃኒዓለም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
