በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የውሃ ቧንቧ ዝርጋታ ዕቃዎች
- የቧንቧ መፍቻዎች
- የጽህፈት መሳሪያዎች
- የጽዳት ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ እና ጫማዎች
- የቢሮ ውስጥ ዕቃዎች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሞተር ሳይክል
- የተለያዩ የመኪና ዘይቶች እና የመኪና ጎማ
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።
- የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው።
- የዘመኑን ግብር የከፈለ።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።
- የቫት እና ቲን (TIN) ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ በጥንቃቄ ታሽገው ፋይናንሻል (financial) አንድ (1) ኦርጅናል፣ ቴክኒካል (technical) አንድ (1) ኦርጅናል፣ (2) ኮፒ ፋይናንሻል (financial) እና (2) ኮፒ (ቴክኒካል (technical) በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ሞጆ ከተማ የሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ሰነዱ ስርዝ፣ ድልዝ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ፣ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው የሚሞላው በነጠላ ዋጋ ነው።
- በተጫራቾች ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ግልጽና አጠራጣሪ ባልሆነ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ባልሆነ ጽሑፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውንም የሃሳብም ሆነ የዋጋ ማሻሻያ በማቅረብ ከጨረታው ውጪ መሆን አይቻልም፡፡
- የሚቀርቡት ዕቃዎች 1ኛ ደረጃ መሆን ይኖርባቸዋል፤ ለማሸነፍ ብሎ ዕቃውን የማይመጥን፣ ያልሆነ ዋጋ ሞልቶ ወይም ሰጥቶ እቃው ሲቀርብ 2ኛ ደረጃ ከሆነ የማንቀበል መሆኑን አስቀድመን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 700 ብር እያንዳንዱ ዝርዝር ላይ በመክፈል በሞጆ ከተማ በሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በግዥ እና ፋይናንስ ዳይሮክቶሬት ቢሮ ቁጥር 7 ክፍል ቀርበው ማግኘት (መግዛት) የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ባላቸው እቃዎች ላይ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ15ኛው ቀን በኋላ በመጀመሪያ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም መ/ቤቱ ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እስከ ሞጆ ከተማ በሚገኘው የኒንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት መጋዘን ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ እና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ጽሕፈት ቤት የዋስትና ደብዳቤ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ አለባቸው።
- የጨረታዉ አሸናፊ በጨረታ መመሪያ በተሰጠው መሠረት ጨረታ አሸናፊነቱ በውስጥ ማስታወቂያ እና በስልክ እንደተገለጸ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የጨረታ ውል በሞጆ ከተማ በሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ጋር መፈራረም አለበት፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈበትን የዕቃ አይነት አሸናፊ መሆኑን ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የዕቃውን ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ ከሚደረገው የግዥ ውል 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ የሚችል መሆኑን መገንዘብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በፖስታውና በሰነዱ ላይ ሕጋዊ ማህተም፣ ስልክ ቁጥር እና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- ሞጆ ከተማ በሚገኘው የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
ስልክ ቁጥር:- 022-236-74-77 / 09-21-81-75-48
የጊንቢቹ ፈንታሌ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
