በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 09 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ-3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ በወረዳ 09 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ-3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ አና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በወረዳ 09 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ-3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 ደንብ ልብስ፣ ሎት 2 ጽዳት፣ ሎት 3 የትምህርት የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 6 ህትመት በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው ጉሙሩክ ባለሥልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ ይኖባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና ለ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ-3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከፋይናንስ ክፍል በአካል መጥቶ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ቁጥር 1 (7000) ሰባት ሺህ ብር፣ ሎት 2. 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ፣ ሎት 3 እና ሎት 4 (6000) ስድስት ሺህ ብር፣ ሎት 5 (8000) ስምንት ሺህ ብር፤ ሎት 6 (1000) አንድ ሺ ብር ሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) በአዲስ አበባ አስተዳደር ኮ/ቀ/ክፍለ ከተማ ስም ማስያዝ ወረዳ 09 በጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ 3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስም ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ የሥራ ሰዓት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩት ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ የዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ መሙላት እና በፖስታ አሽጎ የድርጅቱን ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም፤
- በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በ7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚ አካል በማስያዝ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው። የሚጫረቱ ዕቃዎች 20% ለመቀነስም ለመጨመርም መሥሪያ ቤቱ ሙሉ መብት አለው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዕቃውን ሲያገቡ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ደግሞ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መሆኑን እያሳወቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጦርኃይሎች አካባቢ ሙሉ ወንጌል ቸርች ጎን
በኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ በወረዳ 09 የጄኔራል ዋቆ ጉቱ ቁ-3 ቅደመ 1ኛ፣ 1ኛ አና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
