የሲዳማ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ ለስራ አገልግሎት የሚውለውን ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ 02/2018
የሲዳማ ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለመ/ቤቱ ለስራ አገልግሎት የሚውለውን ከዚህ በታች በሎት የተገለጹ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች
በዚሁ መሠረት
- በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የዘመኑን ግብር የነበረ
- የቫት /VAT/ የተመዝጋቢነት ሰርትፊኬት ያለው
- የግብር ከፋይ /TIN NO/ መለያ ቁጥር ያለው፤
- የእቃና የአገልግሎት አቅራቢነት ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል ድርጅት፤
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሰውን ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለስልጣን በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000347602028 በማስገባት እስሊፕ ይዞ በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 208 በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ በCPO /Bid Bond/ የ90 ቀን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒ 2 በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸል፡፡ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጂናል 1 እና ኮፒ 1 በተለያየ በሰም በታሸገ ፕስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታ ቀናት አየር ላይ ይውላል፡፡ ከ15 ቀን በኋላ በ16ኛው ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4፡45 ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል /የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ዕቃውን በራሱ ወጪ አጓጉዞ መጋዘን ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታው መመሪያ መሠረት የጨረታ አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ይገለጻል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 5584
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት
