Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Addis Ababa Driver and Vehicle Licensing and Control Authority (በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- አሽ/ተሽ/ፍ/ቁ/ባ/መግዳ/2018/001

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሎት 1 - የደንብ ልብሶች፣                                                    ሎት 6 - የአይሲቲና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣

ሎት 2 - አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣                           ሎት 7 - ጀኔሬተርና ቴሌቪዥን፣

ሎት 3 - የፅዳት ዕቃዎች፣                                ሎት 8 - ሌሎች ቁሳቁሶች፣

ሎት 4 - የማስታወቂያና የህትመት እቃዎች፣                   ሎት 9 - ፈርኒቸር፣

ሎት 5 - የመኪና ዕቃዎች፣                              ሎት 10 - የእድሳትና ጥገና ዕቃዎች፣

  • ንግድ ምዝገባ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (ቲን ነምበር)፤ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፤ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ሰርተፊኬት ለእያንዳንዱ ሎት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና መስሪያ ቤት መክሊት ህንፃ 8ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 804 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ገዝታችሁ መውሰድ ትችላላችሁ።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት ለእያንዳንዱ ሎት በተናጥል (ለየብቻ) በባንክ የተረጋገጠ CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ለሎት1፣2፣3፣4፣5፣8 እና10 ለእያንዳንዳቸው በተናጠል የ10,000 ብር (አስር ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ለሎት 6 - የ200,000 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ለሎት 7 እና 9 ለእያንዳንዳቸው በተናጠል የ100,000 ብር (አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO አሰርታችሁ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
  • ባለስልጣን መስሪያ ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ውይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡- ከጎላጎል ታወር ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ መከሊት ህንፃ 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር (708) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-67-23-36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን

 

Save Tender