የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግሥት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ1. ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018ዓ.ም
የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመንግሥት መደበኛ በጀት በተገኘ ገንዘብ በቂ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1/ የሠራተኛ ደንብ ልብስ
ሎት 2/ የሠራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት
ሎት 3/ የቢሮ የጽሕፈት አላቂ እቃዎች
ሎት 4/ አላቂ የትምህርት እቃዎች
ሎት 5/ የህትመት ሥራዎች
ሎት 6/ የህክምና አላቂ እቃዎች
ሎት 7/ አላቂ የጽዳት እቃዎች
ሎት 8/ ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 9/ ቋሚ ፈርኒቸር እቃዎች
ሎት 10/ ፕላን ማሽነሪ ጥገና
ሎት 1/ የተለያዩ ጥገና
ሎት 12/ መጽሐፍት
በዚህ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች መሟላት አለባቸው።
- በሙያው ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፡፡
- የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የዚህን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በየሎት ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል ለቋሚ እቃ በየሎት ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) እና ለሌሎች አላቂ እቃዎች በየሎት ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በሁሉም ሎቶች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚያቀርቡትን ዋጋ በክፍል አራት፤ ስድስት እና ዘጠኝ ላይ መሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋና እና ኮፒ በት/ቤቱ ፋይናንስና ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት በየሎት የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ 9 ቁጥር ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት እና ወዛደር የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ዋጋው ፀንቶ የሚቆየው አሸናፊው ከተለየበት ቀን አንስቶ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
- በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ በሚያመርቱት ምርት ከሆነ ሰነዱ በነጻ የሚወስዱ ይሆናል በማያመርቱት ምርት ላይ ሰነድ የሚጋዙ ይሆናል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ባሸነፉበት የእቃ ርክክብ የሚደረግበት ሰዓት 2፡30 እስከ 6፡00 ቴክኒክ ኮሚቴዎች መኖራቸውን አረጋግጦ ማምጣት አለበት፡፡
አድራሻ፡- ልዩ ቦታ ከሰሜን ሆቴል ከፍ ብሎ ከዜና አገልግሎት በስተጀርባ ዶሮ ተራ
በስልክ ቁጥር: 0111 71 22 00 እና 0111 55 07 24 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- በተጠየቁበት እቃ ሳንፕል ያላቀረበ ነጋዴዎች ጨረታቸው ውድቅ ይሆናል፡፡
አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 04 የኢትዮጵያ ትቅደም ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
