በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 08 በሻሌ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት-1 የጽሕፈት ዕቃዎች፤ ሎት-2 የፅዳት ዕቃዎች፤ ሎት-3 የትምህርት ዕቃዎች፤ ሎት-4 የደንብ ልብስ፤ ሎት-5 የሕክምና ዕቃዎች፤ ሎት-6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሎት-7 ፈርኒቸር፤ ሎት-8 የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ት/ጽ/ቤት በሻሌ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 08 በሻሌ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት-1 የጽሕፈት ዕቃዎች፤ ሎት-2 የፅዳት ዕቃዎች፤ ሎት-3 የትምህርት ዕቃዎች፤ ሎት-4 የደንብ ልብስ፤ ሎት-5 የሕክምና ዕቃዎች፤ ሎት-6 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ ሎት-7 ፈርኒቸር፤ ሎት-8 የህትመት ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
ሎት-1 የጽሕፈት ዕቃዎች 21,000 ብር
ሎት-2 የፅዳት ዕቃዎች 20,000 ብር
ሎት-3 የትምህርት ዕቃዎች 20,000 ብር
ሎት-4 የደንብ ልብስ 20,000 ብር
ሎት-5 የህክምና ዕቃ 5,000 ብር
ሎት-6 ኤሌክትሮኒክስ 38,000 ብር
ሎት-7 ፈርኒቸር ቋሚ ዕቃዎች 40,000 ብር
ሎ7-8 ህትመት 6,000 ብር
- የጨረታ ሰነድን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 01 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 11 (አስራ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መሥሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ አለበት።
- መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የጠጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ስሙ ሰሚት ፍርድ ቤት ወደ ቀኝ ገባ ብሎ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር:- 0116-68-12-43
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ት/ጽ/ቤት
በሻሌ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
