የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ ለተሽከርካሪ እና ማሸነሪ አገልገሎት የሚውል ጎማ፣ ባትሪ እና ዘይት ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት መግዛት ይፈልጋል።
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ለድርጅቱ ለተሽከርካሪ እና ማሸነሪ አገልገሎት የሚውል ጎማ፣ ባትሪ እና ዘይት ከዚህ በታች በተቀመጠው መሰረት መግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1 ለተሽከርካሪ እና ማሽነሪ አገልገሎት የሚውል ጎማ
- ምድብ 2 ለተሽከርካሪ እና ማሽነሪ አገልገሎት የሚውል ባትሪ
- ምድብ 3 ለተሽከርካሪ እና ማሽነሪ አገልገሎት የሚውል ዘይት አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 13 ማስገባት አለባችሁ፡፡
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የነበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። የተወዳደሩ ተጫራቾች ያሸነፉትን ድርጅቱ ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋውን 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ጎማ፣ ባትሪና ዘይት በባለሙያ ተረጋግጦ ማለፍ አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች አሽናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0920514407 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በምስ/ጎጃም ዞን በደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት
