Tender Detail

Tender Details


በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 አየር አምባ ቅድመ 1ኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቁሳቁስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 አየር አምባ ቅድመ 1ኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


 

በግልፅ የወጣ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ግልጽ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2018

 

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 አየር አምባ ቅድመ 1ኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ቁሳቁስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 

ሎት

ሎት ዝርዝር

የብር መጠን

ሎት

ሎት ዝርዝር

 

ሎት 1

አላቂ የቢሮ እቃዎች

11,155

ሎት 13

ውሃ ባለ ግማሽ ሊትር

16,657

ሎት 2

የፅዳት እቃዎች

13,135

ሎት 14

ልዩ ፍላጎት ዕቃዎች

10,000

ሎት 3

የደንብ ልብስ

10,350

ሎት 15

ቆሎ

16,657

ሎት 4

የደንብ ልብስ እና የመጋረጃ ስፌት

10,350

ሎት 16

የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ጥገና

13,000

ሎት 5

ህትመት ስራዎች

10,000

ሎት 17

ቤተ መፅሀፍት

10,000

ሎት 6

ህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ ዕቃዎች

13,800

ሎት 18

ቤተ-ሙከራ እቃዎች

11,672

ሎት 7

ኤሌክትሮኒክስ እና ICT እቃዎች

11,500

ሎት 19

የህንፃ ቁሳቁስ

10,507

ሎት 8

የስፖርት እቃዎች

11,672

ሎት 20

የካፍቴሪያ እድሳት ግሪል እና ፓርቲሽን ስራ

20,074

ሎት 9

የትምህርት ዕቃዎች

11,672

 

 

 

ሎት 10

የትራንስፖርት አገልግሎት

11,672

 

 

 

ሎት 11

የጭነት አገልግሎት

3,000

 

 

 

ሎት 12

አላቂ የህክምና ዕቃዎች

3,000

 

 

 

 

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘርዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ።
  2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር አቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ።
  3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ።
  5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው
  6. ጨርታ ሰነዱ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 07 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል ።
  7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ለዚሁ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  8. ጨረታው በ10ኛ ቀን ከቀኑ 10፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ የሚቀጠለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉትን ዋጋ የውል ማስረከቢያ 10% ማሲያዝ አለባቸው
  10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርቡባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ። ናሙና የማይቀርብባቸው እቃዎች መ/ቤቱ ባቀረበው እስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
  11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት 2፡30 እስከ 9፡00 ማቅረብ ይኖርበታል።
  12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እሰከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ:- ቦሌ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጎን ወደ ነዳጅ ማህበር

ስልክ ቁጥር 011-888-06-48 በተጨማሪ 0906-06-44-71

 

በቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 01 አየር አምባ ቅድመ 1ኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

 

Save Tender