Tender Detail

Tender Details


በቦሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የት/ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የጥገና ዕቃዎች፣ ሎት 6 የደንብ ልብስ እና የጫማ፣ ሎት 7 ደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 0001/2018 ዓ.ም

 

በቦሌ ክ/ከተማ ት/መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 አላቂ የት/ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የጥገና ዕቃዎች፣ ሎት 6 የደንብ ልብስ እና የጫማ፣ ሎት 7 ደንብ ልብስ ስፌት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳታፍ የሚፈልጉ።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና በመንግስት የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቁጥር 5 /አምስት/ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን ብር ሎት 1 አላቂ የት/ዕቃዎች እና የተለያዩ የፅ/መሳሪያዎች 4,000.00 /አራት ሺህ ብር / ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች 6,000.00 /ስድስት ሺህ ብር/ ሎት 3 ቋሚ ዕቃዎች 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/ ሎት 5 የጥገና ዕቃዎች 4,000.00 /አራት ሺህ ብር/ ሎት 6 የደንብ ልብስ እና ጫማ 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 7 ደንብ ልብስ ስፌት 2000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ በቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምረው በመሙላት የጨረታውን ሰነድ ኦሪጂናልና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገና ማህተም ባረፈበት ኤንቨሎፕ በማድረግ በት/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በአስረኛው ቀን በ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያውና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በቴክኒክ ፍላጎት የሚገመገም ይሆናል፡፡
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ውል በሚዋዋሉበት ወቅት ላሸነፉበት ዕቃ የሚውል የውል ማስከበሪያ 10% CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ት/ቤቱ በዕቃዎች ላይ 20% የመጨመር መብት አለው፡፡
  10. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የሚገኝ ሲሆን ልዩ ቦታ ቦሌ ሆምስ

ስልክ ቁጥር:- 011-8-22-25-11

 

ቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የቦሌ ህብረተሰብ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

 

Save Tender