Tender Detail

Tender Details

  • Deadline19 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ሎት 3 ብር 45,000 /አርባ አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Electronics Materials

በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግስት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ላሉት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018

 

በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግስት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ላሉት ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡-

ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች

ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች

ሎት 2 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  2. ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ ተጫራቾች ለሎት 1 የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ሃምሣ ብር/፣ ለሎት 2 የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሣ ብር/፣ ለሎት 3 የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ እየከፈሉ ከሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ የእያንዳንዱን ዕቃ ነጠላ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ለእያንዳንዱ ሰነድ ቢያንስ ሁለት ሁለት ኮፒ አድርገው በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. እያንዳንዱ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በየሎቱ ሲሆን ከስራ ፈቃዳቸውና ከተዛማጅ ውጭ መወዳደር አይቻልም፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለሎት 1 ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ሎት 3 ብር 45,000 /አርባ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ታሽጎ በተመሣሣይ ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመከፈት ሂደት እያስተጓጉልም።
  7.  የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት ውል በመግባት ውል ከገባበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በውሉ መሠረት ዕቃዎችን በወረዳው ፋይ/ጽ/ቤት/ሺሺንዳ ከተማ ድረስ በማቅረብ ቆጥሮ ማስረከብ መቻል ይኖርበታል።
  8.  ተጫራቾች የዕቃ ናሙናውን ከጨረታ ፖስታው ጋር እስከ ወረዳው ርዕሰ ከተማ ፋይ/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ የጨረታ ፖስታ ተከፍቶ የጨረታው አሸናፊ ሲታወቅ ጨረታውን ያላሸነፈ ወዲያው ተመላሽ ተደርጎለት የሚወስድ ሆኖ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያመጣውን ናሙና በአደራ አስቀምጦ መሄድ መቻል ይኖርበታል።
  9.  አሸናፊው ድርጅት ያቀረበው ዕቃ ጥራቱና መጠኑ የተጓደለ ከሆነ በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  10. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው (CPO) ለተሸናፊው ወዲያውኑ የሚመለስ ሲሆን አሸናፊው ማሸነፉ ከተለጸበት ቀን አንስቶ እስከ 5ኛው ቀን ድረስ የውል ማስከበሪያ አስይዞ ውሉን የማይፈፅም ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0476680200/0431 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡

 

በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክልላዊ መንግስት በካፋ ዞን የሺሾ እንዴ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት

 

Save Tender