በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የየካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 7500.00
- ሎት 3 የስፌት የእጅ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00
- ሎት 4 አላቂ የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
- ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
- ሎት 6 የቤተሙከራ ኬሚካሎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2500.00
- ሎት 7 የቧንቧ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000.00
- ሎት 8 ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00
- ሎት 9 የካፌ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00
- ሎት 10 የትራንስፖርት አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
- ሎት 11 የተለያዩ ጥገናዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ናሙና (ሳምፕል) ለሚፈለግባቸው ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ ማስረጃ የሚያቀርብ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
- በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ 10% (ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ላይ በተጠቀሰው የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚህ ተብሎ ለተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ሲሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ወቅት ከሚመለከተው አካል ወቅቱን የጠበቀ በጽሕፈት ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም መወዳደር የሚችሉት በራሳቸው በተመረተ ምርት ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 – 10፡00 ሰዓት ድረስ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ለ10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን በ3፡00 /ሶስት/ ሰዓት ታሽጎ በ3፡30 /ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የገዛችሁትን ሙሉ ሰነድ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አብራችሁ ማስገባት አለባችሁ፡፡ ሙሉ ሰነዱን ያላስገባ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
- የግዥ ውል በሚፈፀምበት ወቅት መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተመለከተው የዕቃ ብዛት እስከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112768120/0112303241/0112303054 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አውቶብስ ተራ ወደ መሳለሚያ በሚወስደው መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኮልፌ ቅርንጫፍ አጠገብ የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የካቲት 23 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
