በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የአፄ ነአኩ ቶለአብ ቅ/አ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የአፄ ነአኩ ቶለአብ ቅ/አ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ እና በውስጥ ገቢ በጀት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በመጀመሪያ ዙር ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያ ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ፣ የእስፖርት ልብስና እቃዎች እና የስፌት አገልግሎት ፣ ሎት3 ፣ የፅዳት ዕቃዎች ሎት 4 የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሎት5 የኮምፒውተርና፣ ፕሪንተር፣ ኮፒ ማሸን ጥገና፣ ሎት6 የህትመት ሥራዎች፣ ሎት7፤ ቋሚ እቃዎች ሎት 8፣ የጭነት አገልግሎት ሎት 9፣ የአላቂ የትምህርት ዕቃዎች ፣ ሎት10 የላብራቶሪ መገልገያ ዕቃዎች፣ ሎት11 የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች ሎት12፣ የሕንፃ እድሳትና ጥገና ሥራዎች ሎት13 አጋዥ መጽሐፍ ሎት 14 የሻይ ቤት ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል፤ በመሆኑም ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የተጨማሪ እሴት ታክስ /vat 15%/ ተመዝጋቢ የሆናችሁ ፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ዋጋውን ከነቫቱ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የአቅራቢነት የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው አቅርቦቶች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፣
- አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 ብር 7,000 00 /ሰባት ሺህ ፣ ለሎት2 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 3 ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/፣ ለሎት 4 ብር 4,000/ አራት ሺህ ብር/ ፣ ለሎት 5 ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት 6 ብር 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት7 ብር 12,000.00 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት8 ብር 2,000.00 /ሁለት ሺህ ብር/ ለሎት9 ብር 13,000.00 / አስራ ሶስት ሺህ ብር/ ለሎት 10 ብር 8000.00 / ስምንት ሺህ ብር/ ሎት 11ብር፣ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ሎት 12ብር 4000 /አራት ሺህ ብር/ ሎት13 በብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ ሎት14 በብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ በባንክ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፣ እንዲሁም ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ ልዩ አስተያየት የሚኖረው አምራች በሆኑበት ዕቃዎች ላይ ብቻ ከአደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የመንግሥት የሥራ ቀን ድረስ ከቢሮ ቁጥር 3 ግዥ ክፍል በመምጣት በመንግሥት በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ እስከ 10ኛው የመንግሥት የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግሥት የሥራ ሰዓት በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 3 አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና እና የመ/ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 2 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን 11:00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3:30 ላይ በቢሮ ቁጥር 2 ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት የአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና /መ/ደ/ት/ቤት ንበረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ናሙናዎችን ቀድመው ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾችን ከመረጠ በኋላ ለሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ7 (ሰባት) የቅሬታ ቀን በኋላ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10% ለግዥ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል፣ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚደረግ ይሆናል፡፡
አድራሻችን፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አፍንጮ በር አደባባይ ወደ መነን የሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ አፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ አንደኛና እና መ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118704592 /0111261456
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 የአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅ/አ/አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት
