በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
ሎት 1 - ለጽህፈትና የትምህርት መሳሪያዎች 51,871.94 /ሃምሳ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ሰባ አንድ ብር ከዘጠና አራት ሳንቲም/፤
ሎት 2 - ለጽዳት ዕቃዎች 42,609.82 /አርባ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠኝ ብር ከሰማንያ ሁለት ሳንቲም ብቻ)፤
ሎት 3 - ለደንብ ልብስ ዕቃዎች 33,000 /ሰላሳ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/፤
ሎት 4 - ለስፖርት ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፤
ሎት 5 - ለኤሌክትሪክና የህንጻ እቃዎች 9,896 /ዘጠኝ ሺህ ስምንት መቶ ዘጠና ስድስት ብር/፤
ሎት 6 – ለአላቂ የህክምና ዕቃዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ/፤
ሎት 7 - ለማሽነሪ ጥገና አገልግሎት 2,100 /ሁለት ሺህ አንድ መቶ ብር ብቻ/፤
ሎት 8 - ለደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት 1,500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/፤
ሎት 9 - ለህትመት ስራዎች አገልግሎት 2,000 /ሁለት ሺህ ብር/፤
ሎት 10 - ለጉልበት እና ትራንስፖርት አገልግሎት 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/፤
ሎት 11 - ቋሚ እቃ 16,000 /አስራ ስድስት ሺህ ብር/፤
ሎት 12 - የግቢ ውስጥ ጥገና 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ)፤
ሎት 13 - የት/ቤቱ ክበብ እና የተማሪ ክበብ ለማከራየት 24,000 (ሃያ አራት ሺህ ብር) በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- በሁለትና ከዛ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ማስረጃ በማያያዝ በተለያየ ፖስታ በማሸግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የተሟላ ማስረጃ የሌለው ሎት ውድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 በሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
- በመንግስት የተደራጁ ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው ድርጅቶች በድጋፍ ደብዳቤ መሳተፍ የሚችሉት እራሳቸው ባመረቱት እቃዎች ላይ ብቻ ነው።
- ት/ቤቱ ከሚገዛው ዕቃ ግዢ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት።
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የግዢውን አይነትና የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ ዋናውንም ኮፒውንም የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦሪጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ፖስታውን ሲያስገቡ ናሙና ለሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙናዎች መግባት አለባቸው።
- ትምህርት ቤቱ ካስቀመጠው ተፈላጊነት /specification/ አንሰው ወይም በልጠው የሚመጡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸው።
- የትምሀርት ቤቱን የጨረታ መመሪያ ክብ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከፖስታው ጋር ማስገባት አለባችሁ።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ጠቅላላ የዕቃውን መጠን 25% እስከ 6 ወር ድረስ ተጨማሪ ቢጠየቅ በራሱ ዋጋ የሚያቀርብ ይሆናል።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ቶታል ፊት ለፊት ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር:- 011-2-59-55-94/011-2-59-34-38/40
የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
