በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
1ኛዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች
1 የደንብ ልብስ ግዥ 2 ለአላቂ የቢሮ እቃዎች
3 አላቂ የት/ት እቃዎች 4 አላቂ የጽዳት እና ሌሎች ዕቃዎች
5 ለተለያዩ አላቂ እቃዎችና አቅርቦቶች 6 ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
7 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 8 የተለያዩ አጋዥ የትምህርት መፃህፍት ህትመቶች እና የላብራቶሪ እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውን ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርብ፣
- የገቢዎች እና ጉምሩከ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት /ቫት/ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ማያያዝ የሚችሉ መሆን አለበት
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 ሺ ብር በባንክ በተረጋገጠ C.P.O. ማስያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት /ንብረት ክፍል /ድረስ መጓጓዣና የመገጣጠሚያ ዋጋ አካትተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የመወዳደሪያ ዋጋው ከነቫት በማስቀመጥ በግልጽ ተጠቅሶ መጻፍ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና /specification/ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከታወቀ በኋላ በ15 ቀናት ውስጥ ከት/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል አለበት።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ደረጃውን የጠበቀ ዕቃዎችን ትዕዛዙ በደረሳቸው በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ በናሙናው መሰረት አጠናቀው ለት/ቤቱ ንብረት ክፍል ሲያስረክቡና በጥራት ኮሚቴ ተፈትሾ ሲያልፍና በተቋሙ ኃላፊ ገቢ እንዲሆን ከታዘዘ በኋላ ይከፍላቸዋል፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 የጨረታው ሳጥን ይታሸግና በዛው እለት በ4፡30 ሰዓት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋ/ግ/ንብ/አሥ/የቡድን መሪ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ሊታወቅ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈበት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ C.P.O. በቅድሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአያት አደባባይ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል በመናፈሻ ፊት ለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ - በስልክ ቁጥር ፡- 0911989727
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሚኩራ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ቦሪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
