ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልገሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
MOTITE FURA PRIMARY HOSPITAL (ሞቲቴ ፉራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል)
የጨረታ ማስታወቂያ
ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለተለያዩ አገልገሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት
ሎት 1 - ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
ሎት 2 - እስቴሽነሪ እቃዎች ግዥ
ሎት 3 - የጽዳት እቃዎች ግዥ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም
- ተጫራቾች በመስኩ የ2017 ዓ.ም የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000372939398 በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰአት ሞቲቴ ፉራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በፈለቀች ሆቴል በኮብልስቶን ገባ ብሎ በሚገኘው ሆስፒታል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የሥራ ቀናት እሁድ እና ቅዳሜን ሳይጨምር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ከምሳ ሰአት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ከሎት 1 እስከ 3 ላለው ብር 20,000 (ሃያ ሺ) ብር ሕጋዊ ከሆነው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በጥሬ ማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውና (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒ (ቴክኒካል) ሰነዶቹን ለየብቻ በታሸጉ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
- ጨረታውን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰአት ታሽጎ በእለቱ 9፡00 ሰአት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ በዓል ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ድርጅት እቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት ሆስፒታል ድረስ በማምጣት የማቅረብ ግዴታ አለበት ፡፡
- ሆሰፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462200046 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ሞቲቴ ፉራ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
