በአራዳ ክ/ከተማ የበሔራዊ ቤተ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 የበጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት ' የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት 5 ሎት 9 የኮምፒዩተር ጥገና እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
አራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሔራዊ ቤተ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-01/2017 ዓ.ም
በአራዳ ክ/ከተማ የበሔራዊ ቤተ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት ለ2018 የበጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ ሎት ' የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት፣ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 4 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት 5 ሎት 9 የኮምፒዩተር ጥገና እንዲሁም የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል። በጨረታ መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
-
ተጫራቾች በተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
-
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ሰርተፊኬት) ያላቸውና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200፡00/ሁለት መቶ ብር / በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ አይነት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
-
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% በት/ቤቱ ስም (በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ) በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከመወዳደሪያ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለባቸው።
-
ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
-
በሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ VAT 15% ተሰልቶ መካተት ይኖርበታል፣ ይህ ካልሆነ ግን VAT እንደተካተተበት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
-
ተጫራቾች የዝዙትን የጨረታ ሰነድ አሪጅናል ላይ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ላይ ማህተም በማድረግ ከ ኮፒ ጋርበፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
-
የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመከፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
-
ተጫራቾች የፎቶ ናሙናዎችን በፖስታ በማሸግ እና ማህተብ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ውጪ ለብቻው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
መ/ቤቱ የሚጫረተውን ዕቃ ብዛት እንደ አስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
-
ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉልበት ወጪ ለተቋሙ ገቢ ማድረግ አለባቸው።
-
የተሰረዘ እና የተደለዘ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
-
ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 011-8-12-01-30/ 011-1-11-83-94/ 011-1-70-50-50 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ አድራሻ፡- በአራዳ ከ/ከተማ ወረዳ 06 ናዝሬት ት/ቤት ወረድ ብሎ
የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የብሔራዊ ቤተ መንግስት የመ/ደ/ት/ቤት
